top of page

ጥር 8፣ 2015- የሱዳን ወታደራዊ መንግስት መሪ ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን የአገሪቱን ፖለቲከኞች በወታደራዊ ጉዳዮች ጣልቃ አትግቡብን አሉ

  • Jan 16, 2023
  • 1 min read

የሱዳን ወታደራዊ መንግስት መሪ ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን የአገሪቱን ፖለቲከኞች በወታደራዊ ጉዳዮች ጣልቃ አትግቡብን አሉ፡፡


አልቡርሃን ፖለቲከኞቹ በየራሳቸው ማህበራት ማሻሻያ ላይ ሊያተኩሩ ይገባል ማለታቸውን አናዶሉ ፅፏል፡፡


ወታደራዊ መሪው ፖለቲከኞቹ ይፈፅሙታል ያሉት ጣልቃ ገብነት በዝርዝር አልተጠቀሰም፡፡


አል ቡርሃን በበኩላችን በጦር ሀይላችን ውስጥ ፅንፈኞች ሰርገው እንዳይገቡ እንከላከላለን ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


በሱዳን በግልበጣ ስልጣን የያዙት የጦር አለቆች ቀደም ሲል አገሪቱን ወደ ሲቪል አስተዳደር ለማሸጋገር ከተለያዩ የፖለቲካ ወገኖች ጋር ስምምነት ፈርመዋል፡፡


ሽግግሩ ለ2 አመታት እንደሚዘልቅ ታውቋል፡፡


ስምምነቱ ቢፈረምም ሱዳን አሁንም ከፖለቲካዊ ቀውሷ እንዳልተላቀቀች ይነገራል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

Recent Posts

See All
በ'ፊንቴክ' የማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች ላይ ፖሊስ የጠየቀው የተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ላይ ለመወሰን ፍርድ ቤት ለነገ ቀጥሯል።

ከ"ፊንቴክ" (Fintech) ኢንቨስትመንት ጋር በተያያዘ በከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች ዛሬ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። መርማሪ ፖሊስ በቀሪ የምርመራ ስራዎች ምክንያት ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page