የኤሌክትሮኒከስ ምርቶች ከሚያቀርቡ ታላላቅ የሞባይል አምራች ኩባያዎች አንዱ በሆነው ትራንሽን ኩባንያ የሚመረተዉ አይቴል ሞባይል አዲስ ስሪት ምርቱን ይፋ አደረገ፡፡
አዲስ ስሪቱ የአይቴል ሞባይል ቀፎ የላቁ የሆኑ ፈጠራዎችን የያዘ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ስያሜውም አይቴል A70 ሞዴል ተብሏል፡፡
የረቀቀ የካሜራ ቴከኖሎጂ የተገጠመለት አይቴል A70 ሞዴል የሞባይል ስልክ ቀፎ የፊት ለፊት 8 ሜጋ ፒክስል እንዲሁም ዋናው የኃላ ካሜራ 13 ሜጋ ፒክስል ካሜራ መሆኑ ተነግሮለታል፡፡
ይህም ጥራት ያላቸውን ምስሎች በዝቅተኛ ብርሃን ውስጥም ሆነ በርቀት በጥራት እና ቀለማትን ቁልጭ አድርጎ ማንሳት የሚያስችል አቅም አለው ተብሎለታል፡፡
4+8 ጂቢ ራም ከ128 ጂቢ የሜሞሪ፣ ባለ 5000 ሚሊ አሚፒር ባትሪ እንደተገጠመለት ሰምተናል፡፡
ከ10 ዓመታት በፊት የተመሰረተው እና በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ በትራንሽን ማኑፋክቸሪንግ ኩባንያ ስር ተመዝግቦ በኢትዮጵያ ከሚገጣጠሙ የሞባይል ቀፎ ኩባንያዎች መካከል አይቴል ሞባይል አንደኛው ነው፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Kommentare