top of page
  • sheger1021fm

ጥር 6፣ 2015- በደብረብርሃን ከተማ አለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ንግድ እና ፋይናንስ ኤክስፖ ዛሬ ተከፈተ


በደብረብርሃን ከተማ አለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ንግድ እና ፋይናንስ ኤክስፖ ዛሬ ተከፈተ።


የደብረብርሀን ከተማ አስተዳደር ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር ያተዘጋጀው ኤክስፖ ከጥር 6 እስከ 14፣ 2015 ዓ.ም እንደሚቆይ ሰምተናል።


በመክፈቻ መረሀግብሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የተለያዪ ሀገራት ዲኘሎማቶችና አንባሳደሮችን ጨምሮ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።


ዛሬ በደብረብርሃን በተከፈተው ኤግዚቢሽን ላይም ኢንቨስተሮች፣ አለም አቀፍ ተቋማት፣ ነጋዴዎች እና አምራቾች ተሳትፈዋል ተብሏል።


በመረሀግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ካሳሁን እምቢአለ እንዳሉት በሚቀጥሉት 10 ዓመታት በአፍሪካ ውስጥ ከሚጠቀሱት 10 ኤክስፖዎች መካከል የደብረብርሀንን ኤክስፖን ተጠቃሽ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል።


የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፍአለ በበኩላቸው አምራች ኢንዱስትሪዎች በክልሉ በሚፈለገው መጠን አለመኖሩን ጠቅሰው ባለሀብቶች በስፋት ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተናግረዋል።


በተጨማሪም ለኢንቨስትመንት ዘርፉ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር መንግስት ስራዎችን እየሰራ ነው ብለዋል።


ለ9 ቀናት የሚቆየው ኤክስፖ በክልሉ ያሉት አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርታቸውን የሚያስተዋውቁበት፣ አዳዲስ ባለሀብቶች ወደ ክልሉ የሚገቡበትን ምቹ ሁኔታ እንዳለ ለማሳየት ያለመ እንደሆነም ሰምተናል።


ፋሲካ ሙሉወርቅ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

Recent Posts

See All

በኢትዮጵያ የካፒታል ወይም ድርሻዎች ገበያ መሳተፍ ለሚፈልጉ ተቋማት ከ3 እስከ 6 ወር ባለው ጊዜ ፍቃድ መስጠት ይጀመራል ተባለ። ፍቃድ የሚሰጣቸውን ተቋማት ለመለየት መመሪያ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ታዬ ተናግረዋል። የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ የተመለከተ ምክክር

በጋሞ ዞን ውስጥ የሚገኙ የዘይሴ እና የቁጫ ብሔረሰቦች ከፍተኛ በደል እየደረሰባቸው ነው ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑ እንደራሴዎች ተናገሩ፡፡ ለሚደርሰው በደል ዋነኛው ምክንያት የአካባቢው ነዋሪዎች በምርጫ ወቅት የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲን በመምረጣቸው ነው ብለዋል፡፡ ንጋቱ ሙሉ ሸገርን ወሬዎች፣ መ

በአፋርና በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት የወደሙ ት/ቤት መልሶ መገንቢያ እስካሁን 2.8 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል ተባለ፡፡ በጦርነቱ ከ300 ት/ቤቶች በላይ ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ይታወሳል፡፡ ተመስገን አባተ ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

bottom of page