top of page

ጥር 6፣ 2015የሊባኖስ ጦር የእስራኤል ሰው አልባ የቅኝት በራሪ አካል (ድሮን) የአየር ክልላችንን ጥሶ ገብቷል አለ

  • sheger1021fm
  • Jan 14, 2023
  • 1 min read

የሊባኖስ ጦር የእስራኤል ሰው አልባ የቅኝት በራሪ አካል (ድሮን) የአየር ክልላችንን ጥሶ ገብቷል አለ፡፡


የእስራኤል ድሮን ወደ ደቡብ ሊባኖስ ዘልቆ መግባቱን የጦሩ ሹሞች እንደተናገሩ ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡


ድሮኑን ለመምታት ብንሞክርም አልተሳካልንም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


እስራኤል የሊባኖስን የአየር ክልል በተደጋጋሚ እንደምትጥስ ዘገባው አስታውሷል፡፡


የሊባኖስ ጦር የአየር ክልሌ በእስራኤል ድሮን ተጥሶብኛል ስለማለቱ ከእስራኤል በኩል የተሰማ አስተያየት የለም፡፡


ደቡባዊ ሊባኖስ የኢራን ሸሪክ የሆነው የሄዝቦላህ የጦር እና የፖለቲካ ድርጅት ዋነኛ መሰረት መገኛ መሆኑ ይነገራል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page