top of page

ጥር 30 2017 - በአዲስ አበባ አንዳንድ የመንግስት አገልግሎቶችን  በ3ተኛ ወገን ለማሰራት የሚያስችል ደንብ ፀደቀ

  • sheger1021fm
  • Feb 7
  • 1 min read

በአዲስ አበባ አንዳንድ የመንግስት አገልግሎቶችን  በ3ተኛ ወገን ለማሰራት የሚያስችል ደንብ ፀደቀ።


በሶሶተኛ ወገን ለማሰራት የታሰቡት የመንግስት ስራዎች የትኞቹ እንደሆኑ አልተገለፀም።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ተኛ ዓመት 7ተኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ  ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።


ወሳኔ ከተላለፈባቸው መካከል አንዳንድ የመንግስት አገልግሎቶችን በውል ለ3ተኛ ወገን ለማስራት የወጣውን ረቂቅ  ደንብ  ካቢኔዉ ያፅደቀበት ይገኝበታል።

በከተማዉ  አስተዳደር በጀት ተመድቦላቸዉ የተገነቡ እና በመጠናቀቅ ያሉትን  አዳዲስ ሆስፒታሎችን ዘመኑን በዋጀ ህክምና መሳሪያ ለማሟላት እና አለም አቀፍ ደረጃን የሚያሟላ  አገልግሎት መስጠት ያስችላቸው ዘንድ  በዘርፉ ትልቅ ልምድ ካከበቱ የግል ሴክተር ጋር በአጋርነት ለመስራት ዉሳኔ አሳልፏል።


የተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ላላቸው እና ተኪ ምርቶችን ለሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎች ባቀረቡት የማስፋፊያ ቦታ ጥያቄዎች በሙሉ ድምፅ ፅድቋል።


ካቢኔው የኮሪደር ልማት ውጤት ከሆኑት ሥራዎች አንዱ የብዙሀን ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ችግሮች የሚያቃልል እና የትራፊክ ፍስቱን የሚያሻሽለው የብስክሌት መጋራት አገልግሎት እና የብስክሌት መስመር አጠቃቀም ደንብንም  አፅድቋል።

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page