ጥር 30፣2016 - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬተር ሆነው ተሾሙ
- sheger1021fm
- Feb 8, 2024
- 1 min read
ዛሬ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት አቶ ተመስገን ጥሩነህን ተክተው ሬድዋን ሁሴን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሆነው ሲሰሩ የቆዩትን የሬድዋን ሁሴንን አዲስ ሹመት መረጃ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ነው ያወጣው፡፡

በተጨማሪም አቶ ሰለሞን ሶካን በመተካት ትዕግስት ሃሚድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል፡፡
ትዕግስት ሃሚድ የተቋሙ ምክትል ዳይሬክተር ሆነው ሲሰሩ መቆየታቸው ተሰምቷል፡፡

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Commentaires