ጥር 29 2017 - በኢትዮጵያ ያለውን የቤት ችግር ለመፍታት የቤቶች የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ማቋቋም ያስፈልጋል ተባለ
- sheger1021fm
- Feb 6
- 1 min read
በኢትዮጵያ ያለውን የቤት ችግር ለመፍታት የቤቶች የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ማቋቋም ያስፈልጋል ተባለ፡፡
ይህ የተባለው የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የቤት አቅርቦትና ፍላጎትን ለማጣጣም ባስጠናው ጥናት ነው፡፡
ጥናቱን ያጠናው የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ነው፡፡
በኢትዮጵያ ባሉ ከተሞች ያለውን የቤት አቅርቦት ችግር ለመፍታት በአማካኝ በየአመቱ ከ471,000 በላይ ቤቶችን መገንባት ያስፈልጋል ተብሏል፡፡
ጥናቱን ያቀረቡት በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ተመራማሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን ጥላሁን በኢትዮጵያ ያለውን የቤት ችግር ለመፍታት የቤቶች ፋይናንስ ኮርፖሬሽንን ማቋቋም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ለቤት ገንቢዎች የፋይናንስ እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
ተጠሪነቱም ለብሔራዊ ባንክ እንዲሆን ተጠይቋል፡፡
በኢትዮጵያ ያለውን ከፍተኛ የቤት ችግር ለመፍታት መንግስት ከካፒታል በጀቱ 5 በመቶውን እንዲመድብም ተጠይቋል፡፡
አሁን ያለውን የቤት እጦት ችግር ለመፍታት የሪል ስቴት አልሚዎችን የሚያበረታቱ ፖሊሲዎችን መቅረፅ፣ የግሉ ዘርፍ በቤት ግንባታ ዘርፍ እንዲሳተፍ የሚያስችሉ ፖሊሲዎችን ማውጣት፣ የሞርጌጅ ባንኮችን ማቋቋም እንደሚያስፈልግል ተነግሯል፡፡
አሁን ላይ በኢትዮጵያ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑ ቤቶች ከደረጃ በታች መሆናቸውን ተነግሯል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments