477 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መኖር አለመኖራቸወን ማረጋገጥ አልቻልኩም ሲል ተቆጣጣሪው መ/ቤት ተናገረ፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ባለስልጣን ሁለት ጊዜ ጥሪ አቅርቦ ከ 805 ህልውናቸውን ካላረጋገጡ ድርጅቶች 328 ድርጅቶች ቀርበው ምክንያታቸውን ያስረዱ ሲሆን ቀሪዎቹ 477 ድርጅቶች ምክንያታቸውን ማቅረብ አልቻሉም ብሏል፡፡
በአብዛኛው ሪፖርት ያላቀረቡበት ምክንያት በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ ጦርነትና የጸጥታ ችግር እንዲሁም የገንዘብ እጥረት መሆኑን በመግለጻቸው ምክንያታቸውን ተቀብያለሁ ብሏል፡፡
ምክንያት ባላቀረቡት ድርጅቶች ላይ በህጉ መሰረት ለቦርድ አቅረቦ እንዲፈርሱ እንደሚያስወስን ባለስለጣን መ/ቤቱ አስረድቷል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentários