የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ለገበያው ደላሎች፣ ለኢንቨስትመንት አማካሪዎችና ባንኮች ፍቃድ መስጠት እጀምራለሁ አለ።
ገበያው አዲስ እንደመሆኑ የቴክኖሎጂ ግዢና በኢኮኖሚው ውስጥ እንዴት ይከናወን በሚለው በብርቱ ሲሰራ እንደነበር ባለስልጣኑ ተናግሯል።
የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ሥራውን ከመጀመሩ በፊት ያለጥድፊያና በጥንቃቄ ሲሰራ መቆየቱን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ታዬ ተናግዋል።
ከየካቲት 4 ጀምሮ ስቶክ ብሮከሮች፣ አማካሪዎችና የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ የሚሰጣቸው አሁን ለመጀመርያ ግዜ ወደ ሥራ ለመግባት የሚያስችል ማዕቀፍ የሚያሟሉ ሲሆን ነው ተብሏል።
ከዚህ ቀደም በኢኮኖሚ ውስጥ እጅግ አጓጊና የማይመስል የአክስዮን ሽያጭና ግዢ፤ ሥርዓት እንዲይዝ የህግ ማዕቀፍ እየተሰናዳ መሆኑን ባለስልጣኑ ዛሬ ጋዜጠኞችን ጠርቶ ሲናገር ሰምተናል።
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከዚህ ቀደም ፈፅሞ ሐሰት በሆነ መንገድ የአክስዮን ሽያጭና ግዢ የሚያደርጉትን ሁሉ በሚያጠናቅቀው መመሪያና የህግ ማዕቀፉ ወደኋላ ሄዶ ተጠያቂ እንደሚያደርግ እወቁ ብሏል።
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሰነድ መዋለ ነዋይ ገበያ እስከ ባለፈው ታህሳስ ወር ድረስ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች የኢንቨስትመት ተሳትፎ መቀበልና የካፒታል ማሰባሰብ ሥራው እንደሚያጠናቅቅ ተናገሮ ነበር።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የዳሬክተሮች ቦርድ ገበያውን ለመመስረት የሚያስፈልገውን 25 በመቶ ለመጋበዝ መተማመኛም ለመስጠት ወስኖ በኢትዮጵያ ንግድ ህግ መሰረት የተቀመጠውን የአምስት መስራቾች ቁጥር ለማሟላት ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስር ያሉት 4 የልማት ድርጅቶች የኢትዮጵያ የሰነድ ነዋይ ገበያ አክሲዮን መስራች አባል ሆነው የኢትዮጵያ ሰነድ መዋለ ነዋይ ገበያ መቀላቀላቸው ይታወሳል።
ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ጋር በጋራ በመመስረቻው ስምምነት ላይ የፈረሙት ኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ፣ የኢትዮጵያ መድህን ድርጅትና የብርሀንና ሰላም ማተሚያ ድርጅቶች ናቸው፡፡
ማንኛውም የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ኢንቨስትመንት ባንኮችን ለማቋቋም የሚፈልጉ ሁሉ የሚጠበቅባቸውንና ማሟላት ያለባቸውን መስፈርት እስካሟሉ ድረስ ለምን ያህል ይሰጥ የሚለው በገደብ የተቀመጠ እንዳልሆነ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments