የኢትዮጵያን ቡና በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስታወዋወቅና የገበያ እድል ለመፍጠር ይረዳል የተባለ ለ4 ቀን የሚቆይ የአፍሪካ ቡና ሳምንት አውደ ርዕይ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፈተ፡፡
በአውደ ርዕይው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ በኢትዮጵያ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከ20 ሚሊየን በላይ ሰዎች በቡና ላይ ሕይወታቸውን መስርተዋል ብለዋል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ የቡና ዋጋ እየቀነሰ ቢመጣም ኢትዮጵያ ግን በ2016 1.4 ቢሊየን ዶላር በ2015 ደግሞ 1.3 ቢሊየን ዶላር አግኝታለች ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ለዚህም ምክንያት በቀደመዉ አሰራር ላይ ማሻሻያ መደረጉ፣ የቁጥጥር ስራው የበረታ መሆኑ እንዲሁም ባለስልጣኑ ከፍተኛ ትኩረት ለቡና ጥራት መስጠቱ ከሚበዙት ጥቂቶቹ ናቸዉ ተብሏል፡፡
መድረኩ የቡና ልማት ላይ ያሉ ተዋንያኖች ገፅ ለገፅ የሚመክሩበትና የሚወያዩበት እንደሚሆን ተሰምቷል፡፡
በአውደ ርዕዩ ላይ የተለያዩ አለም አገራት ቡና ላኪዎች ተቀባዮች እና አርሶ አደሮች ተገኝተዋል፡፡
ይህም ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ቡና እንድታስተዋውቅ እድል ይሰጣል ተብሏል፡፡
በ4 ቀን በሚቆየው አውደ ርዕይ ቡና ላይ ያሉ ችግሮች ምንድናቸው እና እንዴት ይፈታሉ የሚሉ ፁሁፎች ይቀርባሉ ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አገራት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ቡና ጠጪ ያለባት አገር ነች ተብሏል፡፡
በዚህም በአፍሪካ አህጉር ከሚጠጣው ቡና 50 በመቶ የሚሆነው በኢትዮጵያዊያን እንደሆነ ተነግሯል፡፡
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በተያዘው በጀት ዓመት 1.75 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት አስታውሷል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments