top of page

ጥር 28 2017 - ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፉ በተለይ ወጣቶቿ ላይ ብትሰራ በብዙ ታተርፍበታለች ተባለ

ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፉ በተለይ ወጣቶቿ ላይ ብትሰራ በብዙ ታተርፍበታለች ተባለ፡፡


በሀገሪቱ በሚገኙ የአቪዬሽን ማሰልጠኛ ማዕከላት የሌሎች አገር ዜጎች ስልጠና በመውሰድ እየተጠቀሙበት እንደሆነ ተነግሯል፡፡


ኢትዮጵያ በዘርፉ በተለያዩ ማሰልጠኛዎች ያሉ ወጣቶችን በአግባቡ ብትጠቀምበት በሰው ኃይል ብዛት ባለሙያዎችን ለተለያዩ ሀገራት በማቅረብ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኝላት እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያ ይናገራሉ፡፡


በዚህ ረገድ ግን ዘርፉን በአግባቡ እየተጠቀሙበት ካሉ ሀገራት አንጻር #ኢትዮጵያ አልሰራችበትም የሚሉት በኢትዮጵያ የሚሠራው ኤሮቲክ ኩባንያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሄኖክ ንጉሴ ናቸው፡፡


ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መጥተው በሙያቸው ኢትዮጵያ ላይ የሚያገለግሉ ባለሙያዎች አሉ ኢትዮጵያም ብዙ የማሰልጠኛ ማዕከላት ላይ ብትሰራ ብዙ ወጣቶችን አስተምራ በአቪዬሽን ዘርፍ ትጠቀማለች ብለዋል፡፡


ኢንዱስትሪው በኢትዮጵያ ያልተሰራበት በመሆኑም ሀገሪቱ ላይ የተለያዩ አለማቀፍ ተቋማት ገብተው እንዲሰሩ ለማድረግ በግልና የመንግስት አጋርነት ወይም ፐብሊክ (private partnership) ላይ በደንብ ቢሰራ ለስራ እድል ፈጠራውም ይሁን ኢንዱስትሪ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያደርግ መሆኑን አቶ ሄኖክ ይናገራሉ፡፡


በመንግስትና በግል አጋርነት ሰርተው ከፍተኛ ትርፍና #የውጭ_ምንዛሪ ከሚያገኙና በዘርፉ በብዙ ከተጠቀሙበት አገራት ውስጥም የተባበሩት አረብ አምሬትስ፣ ሞሮኮና ቱኒዚያ ይጠቀሳሉ፡፡


ኢትዮጵያም የግሉን የአቪኤሽን ዘርፍ ለውጭ ኩባንያዎች ክፍት አድርጋ ከምታገኘው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ባለፈ የሰለጠኑ ባለሙያዎችንም ላለማቀፍ ተቋማት በማቅረብ እንደምትጠቀምበት ተነግሯል፡፡


ምህረት ስዩም

コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page