ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃ ለጊዜው አገልግሎት አይሰጥም ተባለ።
ወደ በረራ ይዞ መግባት ከሚከለከሉ ቁሶችም መካከል ከመንገደኞች የሚሰበሰብ የሲጋራ መለኮሻ (ላይተር) ጊዜያዊ የማስቀመጫ ስፍራ ውስጥ ጭስ በመከሰቱ ነው አገልግሎቱ የተቋረጠው ተብሏል።

ለመንገደኞች ደህንነት ሲባል ሕንፃው ለጊዜው አገልግሎቱን እንዳቋረጠ አየር መንገዱ ተናግሯል።
በመሆኑም በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ውስጥ መዳረሻዎቻችን የምትጓዙ መንገደኞቻች በዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል ወደ በረራችሁ እንድትሳፈሩ አየር መንገዱ አሳስᎆል።
ከነገ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለመደው የሀገር ውስጥ ተርሚናል አገልግሎት መስጠት እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተናግሯል።
ለተፈጠረው መጉላላት አየር መንገዱ መንገደኞቹን ይቅርታ ጠይቋል።
Comentários