ኢትዮጵያ በግብርና፣ በጤናው፣ በትምህርት ያለባትን ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች በማሳተፍ እየሰራሁ ነው ሲል የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ተናገረ፡፡
ዲያስፖራው በኢትዮጵያ የሚገኙ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች የገንዘብ ችግር ሳይገጥማቸው የማህበረሰቡን ችግር መቅረፍ የሚችሉ ስራዎችን እንዲሰሩ አግዛለሁኝ ብሏል፡፡
ዘመኑ የደረሰበት ቴክኖሎጂ መጠቀም ደግሞ ሌላው የሚበረታታ ተግባር ነው ሲልም ተናግሯል፡፡
እነዚህ ወጣቶች ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተሰባሰቡ እንደሆኑም ሰምተናል፡፡
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ በትምህርት በጤናና በግብርና የሀገሪቱን ችግር ያቃልላሉ ተብለው የተከወኑ ስራዎችን አወዳድሮ የሽልማት መረሃግብርም አከናውኗል፡፡
ከዚህ ቀደም በሌላ ሌላም ስራ ተሰማርቶ እንደነበርና አሁን ጊዜ የሚፈልገው ይሄን በመሆኑ ፊቱን ወደዚ እንዳዞረ ነግሮናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ማርታ በቀለ
コメント