top of page

ጥር 27፣2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች

በአሜሪካ የፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ዩ ኤስ ኤይድ የተሰኘውን የተራድኦ ድርጅት ሊዘጋው ነው ተባለ፡፡

የድርጅቱ ሰራተኞች በዋሽንግተን ዲሲ ወደሚገኘው ዋና ፀህፈት ቤቱ እንዳይገቡ መከልከላቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡

ቢሊየነሩ የአዲሱ መንግስታዊ ተቋማት ውጤታማነት ተከታታይ መስሪያ ቤት የበላይ ኤለን መስክ ይሄን ፕሬዘዳንት ትራፕም የተስማሙበት ነው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

የትራምፕ አስተዳደር ለወጪ ቁጠባ ብዙ የፌዴራል መንግስት ሰራተኞችን የመቀነስ ውጥን እንዳለው እወቁልኝ ካለ ሰነባብቷል፡፡

በሺህዎች የሚቆጠሩ የዩኤስ ኤይድ ሰራተኞች ቀደም ብሎ መባረራቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡

ዩ ኤስ ኤይድ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛው የሰብአዊ እርዳታ አቅራቢ ሆኖ መቆየቱ ይነገራል፡፡

የሩዋንዳው ፕሬዘዳንት ፖል ካጋሜ የአገራቸው ወታደሮች በኮንጎ እንደሚገኙ በጭራሽ እንደሚያውቁ ተናገሩ፡፡

ሩዋንዳ የM-23 አማጺያንን ከመገደገፍ በተጨማሪ በኮንጎ በሺህዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ከቡድኑ ታጣቂዎች ጋር ማሰለፏ በሰፊው እንደሚነገር CNN ፅፏል፡፡

ካጋሜ ግን ወታደሮቻቸው በኮንጎ ኪንሻሣ እንደሚገኙ በፍፁም እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡

ፖል ካጋሜ በፕሬዘዳንትነታቸው የአገሪቱ ጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ናቸው፡፡

በምስራቃዊ ኮንጎ ኪንሻሣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጦርነቱ በእጅጉ መባባሱ ይነገራል፡፡

አማጺያኑ በምስራቃዊ ኮንጎ ኪንሻሣ 2ኛዋ የሆነችውን የጎማ ከተማን በውጊያ ከተቆጣጠሯት ሰንብተዋል፡፡

የቡካቩ ከተማንም ለመያዝ ተቃርበዋል ነው የሚባለው፡፡

አማጺያኑም በፊናቸው በሩዋንዳ ይታገዛሉ መባሉን በቃል አቀባያቸው አማካይነት ማስተባበላቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡

በኮንጎ ኪንሻሣ የጦር ጥቃቱን ሲያፋፍም የሰነበተው የM 23 አማጺ ቡድን የተናጠል የተኩስ አቁም አድርጌያለሁ አለ፡፡

M 23 ባለፈው ሳምንት ጥቃቱ በምስራቃዊ የአገሪቱ ክፍል ትልቋ የሆነችውን የጎማን ከተማ መቆጣጠሩ ሲነገር ሰንብቷል፡፡

በጎማው ውጊያ ከ900 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡

M 23 ተኩስ ያቆምኩት በሰብአዊ ምክንያቶች ነው ማለቱ ተሰምቷል፡፡

የጎማው ጦርነት በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን አፈናቅሏል ተብሏል፡፡

አማጺ ቡድኑ የሩዋንዳ መንግስት ቀጥተኛ ድጋፍ እንዳለው ይነገራል፡፡

ሬውተርስ እንደፃፈው ደግሞ የኮንጎ ኪንሻሣ መንግስት ኃያላኑ በሩዋንዳ ላይ ከቃላት የተሻገረ እርምጃ እንዲወሰዱባት ጠይቋል፡፡

የቡድን 7 አባል አገሮች እና የአውሮፓ ህብረት ቀደም ሲል የM 23 አማጺ ቡድን የከፈተውን ጥቃት ማውገዛቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡

ሩዋንዳም አማጺ ቡድኑን መደገፏን እንድታቆም ጠይቀዋል ኃያላኑ፡፡

የኮንጎ ኪንሻሣ መንግስት በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አማካይነት በሩዋንዳ ላይ ከውግዘት ባለፈ ማዕቀብ ሊጣልባት ይገባል ማለቱ ተሰምቷል፡፡

የኔነህ ከበደ

Comments

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page