በተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት ውስጥ የሚያገለግሉ ሰዎች ገንዘብ ወሰዱ፣ ሙስና ፈፀሙ ሲባል ይሰማል፡፡
በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ የሚፈፀምን #ሙስና ወይም ሌብነት መቆጣጠሪያ መላ ወይም ህግ አለ ወይ?
የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በመንግስት እና ህዝባዊ ተቋማት ላይ የሚደረጉ የሙስና ወንጀሎችን ተከታትዬ ለፍትህ ተቋማት አቀርባለሁ ይላል፡፡
ይሁንና እነዚህ የሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚደረጉ የሙስና ወንጀሎችን የምከታተል ስልጣን እንደሌለው ተናግሯል፡፡
ኮሚሽኑ ከማይመለከታቸው ተቋማት መካከል የሃይማኖት ተቋማት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንዲሁም እድርን የመሳሰሉትን የመመርመር እና የማጣራት ስልጣን የለውም ሲሉ የነገሩን በስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ሻሜቦ ናቸው፡፡
በሀይማኖት ተቋማት የሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎች በህጉ እንዴት ይታያል ስንል የህግ ባለሞያ የሆኑትን አቶ ተጠምቀ ዮሀንስን ጠይቀናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ማርታ በቀለ
Comments