ህጋዊ አይደለም በሚል በፍርድ ቤት የተሻረውና በተለምዶ የጣራና ግድግዳ እየተባለ የሚጠራውን የቤትና ቦታ ግብር ያለቅጣትና ወለድ በጊዜ ክፍሉ ሲል አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አሳሰበ፡፡
በአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ሚያዚያ 3 ቀን 2015 በጻፈው ድብደቤ #የጣራና_ግድግዳ እየተባለ የሚጠራውን የቤትና ቦታ ግብር ሁሉም ክፍለ ከተሞች እንዲሰበስቡ ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡
እናት ፓርቲ ይህንን የፋይናንስ ቢሮን ውሳኔ ሕግን ያልተከተለ፣ የከተማ አስተዳደሩም ባልተሰጠው ስልጣን ነው ስራ ላይ ያዋለው በሚል ውሳኔው እንዲሻር በፍርድ ክርክር ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ #ፍርድ_ቤት ልደታ ምድብ የፌዴራል አስተዳደር ሥነ ሥረዓት ፍትሐብሔር ችሎት የከተማ አስተዳደሩ ያወጣው የጣሪያ እና ግድግዳ ግብር መመሪያን ባልተሰጠ ስልጣን የወጣ ነው፣ ህጋዊም አይደልም በሚል መመሪያውን እንደሻረው ፓርቲው በትናንትናው እለት በሰጠው መግለጫ ተናግሯል፡፡
ምንም እንኳ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ቢሽረውም በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የጣራና ግድግዳ እየተባለ የሚጠራ የቤትና ቦታ ግብር የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ግብሩ ያለቅጣትና ወለድ የሚከፈልበት ጊዜ እየተጠናቀቀ መሆኑን ተገንዝባችሁ ከወዲሁ ግብራችሁን ክፈሉ ሲል ጠይቋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ 429,829 ግብር ከፋዮች የቤትና ቦታ ግብር ክፍያ እንዲፈፅሙ ይጠበቃል ሲል ቢሮው አስረድቷል፡፡
ይሁንና እስካሁን የከፈሉት ከሚጠበቁት ግማሽ ያህሉ ወይም 228,222 #ግብር ከፋዮች ናቸው ተብሏል፡፡
የቤትና ቦታ ግብራቸውን ከከፈሉ ግብር ከፋዮችም 2.24 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ተናግሯል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
Comentários