የኩላሊት ህሙማንን ለማገዝ የተቋቋሙ ማህበራት በጋራ አለመስራታቸው ህሙማኑ ተገቢውን ድጋፍ እንዳያገኙ እያደረጋቸው ነው ተባለ፡፡
በተለይ ለኩላሊት እጥበት የገንዘብ ችግር የሚገጥማቸው ዜጎች የበዙ በመሆናቸው እርዳታ ጠባቂና ድጋፍ ፈላጊ አድርጓቸዋል ማህበራቱ በራሳቸው ተግባብተው በጋራ አለመስራታቸው በቂ ድጋፍ እንዳይገኝ እያደረገ ነው፤ በዚህም የተቸገሩ ህሙማን በጊዜ የህክምና እርዳታ እንዳያገኙ እያደረገ ነው ያሉን የተስፋ የኩላሊት ታካሚዎች ማህበር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ መስፍን አስረስ ናቸው፡፡
የኩላሊት ህመም ላይ ወደ ሶስት አራት የሚደርሱ ማህበራትና ድርጅቶች ይሰራሉ እነዛ አንድ ላይ ሆነው በህብረት ቢሰሩ ችግር አይፈጠርም፤ ህብረተሰቡም ለማን ለመስጠት እንዳለበት አይቸገርም ብለዋል፡፡
ህሙማኑ የሚገጥማቸውን የህክምና ወጪ ችግር ለመቀነስም ማህበሩ ከተለያዩ የመንግስት የህክምና ተቋማት ጋር በመሆን የኩላሊት እጥበት አገልግሎት እንዲያገኙ እያደረገ እንደሆነም ነግረውናል፡፡
ማህበሩ በመንግስት ስር የሚገኙ ሆስፒታሎች ህክምናውን ብዛት ጨምረው ብዙ ሰዎች እንዲታከሙ ለማድረግ ጥያቄ እናቀርባለን ብለዋል አቶ መስፍን፡፡
በዳግማዊ ምንሊክ በቅዱስ ጳውሎስ እና ዘውዲቱ ሆስፒታሎች ባሉ የኩላሊት እጥበት ማዕከላት ላይ አገልግሎቱ እየተሰጠ ነው ተብሏል፡፡
በኩላሊት ህክምና በጎ አድራጎት ላይ የሚሰሩ ማህበራት በጋራ ሆኖ ቢሰሩ የሚደረጉ ድጋፎች ለህሙማኑ ህክምና በቂ የሚሆን ነው ተብሏል፡፡
ተስፋ የኩላሊት ታካሚዎች ማህበር በቋሚነት አርባ ለሚሆኑ አባላቱ ከተቋማት በሚያገኘው ድጋፍ ነጻ የኩላሊትእጥበት ዲያሊስስ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረጉን ተናግሯል፡፡
ለአንድ ጊዜ የኩላሊት እጥበት በግል የጤና ተቋማት እስከ ሶስት ሺ ብር ድረስ ወጪ የሚጠይቅ ሲሆን ይህም በሳምንት ለሶስት ቀናት ያህል የሚደጋገም ነው፡፡
ምህረት ስዩም
Yorumlar