top of page
  • sheger1021fm

ጥር 25፣ 2015የፌዴራል ግብርን በቀላሉ በቴሌ ብር መክፈል የሚቻልበት አገልግሎት ሥራ መጀመሩ ተሰማ


የፌዴራል ግብርን በቀላሉ በቴሌ ብር መክፈል የሚቻልበት አገልግሎት ሥራ መጀመሩ ተሰማ።


ኢትዮ ቴሌኮም በዓመት በቢሊየን የሚቆጠር የፌደራል ግብርን በቴሌ ብር እንዲከፈል ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር ውል አስሯል።


ለገቢዎች ሚኒስቴር የገቢ ግብርንና የግል ሠራተኞች የጡረተኛ መዋጮ የፌደራል ታክስ ክፍያዎችን በወቅቱ ለመሰብሰብ ያግዛል ተብሏል።


የግብር ከፋዮች የክፍያ አማራጮቻቸው ቀላል እንዲሆንና ባሉበት ቦታ ሆነው የፌደራል ግብራቸውን መክፈል እንደሚችሉ ሰምተናል።


የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ሥርዓቱ ከፍተኛ ገንዘብ የሚገላበጥበት በመሆኑ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ከኢትዮጵያ የመረጃ ደህንነት ኤጄንሲ (ኢንሳ) ጋር አብረው መስራታቸውን ተናግረዋል።


በቴሌ ብር ግብይት የሚፈፅሙ ነጋዴዎች ከሚያከናውኑት ግብይቶች ከሰበሰቡት ገንዘብ ላይ ለግብር ክፍያ በቀጥታ መክፈል የሚችሉበት መላ ምቹ ሆኗል ተብሏል።

ይህን አገልግሎት ለማግኘት ደንበኞች www.mor.gov.et በመግባት የኤሌክትሮኒክስ ታክስ አገልግሎት ከመረጡና የሚፈለገውን መንገድ ከጨረሱ በኃላ የገቢዎች ሚኒስቴር የሚሰጣቸውን የሰነድ ቁጥር በመጠቀምና በመያዝ ክፍያቸውን በቀላሉ በቴሌ ብር ማከናወን ይችላሉ።


በዛሬው የጋራ ሥምምነት የገንዘብ ሚኒስቴር ምኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ የገቢዎች ሚኒስቴር አይናለም ንጉሴ፣ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነርና ሌሎችም የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።


ተህቦ ንጉሴ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

Recent Posts

See All

በኢትዮጵያ የካፒታል ወይም ድርሻዎች ገበያ መሳተፍ ለሚፈልጉ ተቋማት ከ3 እስከ 6 ወር ባለው ጊዜ ፍቃድ መስጠት ይጀመራል ተባለ። ፍቃድ የሚሰጣቸውን ተቋማት ለመለየት መመሪያ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ታዬ ተናግረዋል። የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ የተመለከተ ምክክር

በጋሞ ዞን ውስጥ የሚገኙ የዘይሴ እና የቁጫ ብሔረሰቦች ከፍተኛ በደል እየደረሰባቸው ነው ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑ እንደራሴዎች ተናገሩ፡፡ ለሚደርሰው በደል ዋነኛው ምክንያት የአካባቢው ነዋሪዎች በምርጫ ወቅት የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲን በመምረጣቸው ነው ብለዋል፡፡ ንጋቱ ሙሉ ሸገርን ወሬዎች፣ መ

በአፋርና በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት የወደሙ ት/ቤት መልሶ መገንቢያ እስካሁን 2.8 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል ተባለ፡፡ በጦርነቱ ከ300 ት/ቤቶች በላይ ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ይታወሳል፡፡ ተመስገን አባተ ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

bottom of page