top of page

ጥር 23 2017 - የጋዜጠኝነት ሞያ ፈተና ውስጥ በመሆኑ የሚጠበቅበትን ሀላፊነት እየተወጣ አይደለም ተባለ

የጋዜጠኝነት ሞያ ፈተና ውስጥ በመሆኑ የሚጠበቅበትን ሀላፊነት እየተወጣ አይደለም ተባለ፡፡


በኢትዮጵያ የሚዲያውም ሆነ የጋዜጠኛው ነፃነት ምን ድረስ ነው የሚለው እራሱን የቻለ ጥያቄ ነው፡፡


የሀገሬ ሚዲያዎች የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት መወጣት አልቻሉም በሚል ሲተቹ ይሰማል፡፡


ባለሞያዎች ጋዜጠኛው እና ሚዲያው በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ አሳሳቢ ጉዳዮችን አይቶ እንዳላየ እንዲያልፍ ያደረገው ምክንያቶችን ይናገራሉ፡፡


በዚህም የባለቤትነት ጉዳይም፣ የርእዮት አለም ልዩነቶች፣ የመንግስት ጣልቃ ገብነት የሚዲያው ነጻነት ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን ያስረዳሉ፡፡


የዘርፉ ባለሞያዎች እንደሚሉት ሚድያው ለህዝብ ድምፅ መሆን የዲሞክራሲ ሥርዓቱም እንዲበረታ መንግስትንና ህዝቡን የማንቃትና ጉድለቶችን ነቅሶ ማሳየት ይጠበቅበታል፡፡


ይሁንና ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች የተጠቀሱትንና ሌሎችንም ሀላፊነቶችን በአግባቡ ለመወጣት ተስኖታል፡፡


ከዘርፉ የሚወጡ መገናኛ ብዙሃንም መኖራቸው ተሰምቷል፡፡


የመገናኛ ብዙሃን ችግሮች እንዲፈቱ ከአፈናና ከመንግስት ጣልቃ ገብነትም ወጥተው በነፃነት ስራቸውን መከወን እንዲችሉ በሀገራዊ ምክክሩም ጭምር አጀንዳ ሆኖ ሊመከርበት ይገባል ሲሉ በባህዳር እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትን ስነ ተግባቦት መምህራን አሳስበዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…


ማርታ በቀለ



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page