በበጀት ዓመቱ 6 ወራት የሀብት ምንጭ ማረጋገጥ ምዝገባ በፍትህ ተቋማት ክትትል ከማድረግ ጋር ተያይዞ ውስንነት ታይቶበታል ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡
ይህ የተባለው የፌዴራል የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የስድስት ወር የስራ አፈፃፀሙን ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡
በዚህም ውስንነት እና የአፈፃፀም ድክመት ታይቶባቸዋል የተባሉ ጉዳዮች በዝርዝር ቀርቧል፡፡
ተገኝቶባቸዋል ከተባሉት መካከል የአቅም ግንባታ ስራ፡ የበየነ መረብ ስልጠና፡ የከፍተኛ አመራሮች እና የሰራተኞች አቅም ግንባታ ስልጠና፡፡
በፀረ ሙስና ጉዳዮች ትምህርታዊ ውይይቶችን በሚዲያ ከማቅረብ አኳያ፡ ጉድለቶች እንደታዩባቸው ተነስቷል፡፡
ሌላው የሙስና መከላከል ጥናት ስራዎች አፈፃፀማቸው ዝቅተኛና ያልተፈጸሙ እንዳሉም ተነግረዋል።
ከዚህ ቀደም ተጠናክሮ የማይሰጡ የነበሩ አሁን ግን በቋሚነት ከምንሰራው ስራዎች መካከል አንዱ የአቅም ግንባታ ስልጠና ነው ሲሉ የመለሱት የፌዴራልየስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ ናቸው፡፡
የሀብት ማጣራቱ የተጓተተው ተደጋጋሚ የሆነ ማጣራት ስለምናደርግ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ማርታ በቀለ
Comentarios