top of page

ጥር 23፣2016 - ኃይሌ ሆቴሎች እና ሪዞርቶች ዘጠነኛ መዳረሻውን በወላይታ ሶዶ ከፈተ

  • sheger1021fm
  • Feb 1, 2024
  • 1 min read

በሌላ በኩል ሻሸመኔ በተቃጠለብኝ ሆቴል ምንም አይነት ማካካሻ ከመንግስት አልተደረገልኝም ሲሉ ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ተናግሯል፡፡


ወላይታ ላይ ተሰርቶ ዛሬ መከፈቱ የተነገረው የሻለቃ ኃይሌ ሆቴል እና ሪዞርት 1.1 ቢልየን ብር ወጪ ተደርጎበታል የተባለ ሲሆን ባለ 4 ኮኮብ ደረጃ መሆኑንም ተነግሯል፡፡


ከ15 እስከ 500 ሰዎች መያዝ የሚችሉ የስብሰባ ኣዳራሾች እና 107 መኝታ ክፍሎች እንዳሉት ሲነገር ሰምተናል፡፡

ሆቴሉ ለ300 ሰዎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡



ኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች በቅርቡ በጅማ፣ ደብረብርሃን፣ ኮንሶ እና የወደመው የሻሸመኔ ወደ አገልግሎት የሚገቡ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ናቸው ተብሏል፡፡


በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ ላይ ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት ከፍተኛ ውድመት ከደረሰባቸው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ የኃይሌ ሆቴል አንዱ መሆኑ ይታወሳል፡፡


ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ በሻሸመኔ የወደመው ሆቴል መልሶ ስራ እንዲጀምር እየሰራሁ ቢሆንም ከመንግስት እስካሁን ምንም አይነት ድጋፍ አላገኘሁም፣ ማካካሻ ግን እጠብቃለሁ ብሏል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page