
የሶማሊያ የጦር ፍርድ ቤት በአገሪቱ የIS ፅንፈኛ ቡድን የገንዘብ አንቀሳቃሽ ነች በተባለችው ፋርቱን አብዲራሺድ ሐሰን ላይ የ8 ዓመታት የእስር ቅጣት ፈረደባት፡፡
ሴትዮዋ የሶማሊያው የIS ቡድን ቅርንጫፍ መሪ አብዱቃዲር ሙአሊም ሙሚን ባለቤት እንደሆነች አናዶሉ ፅፏል፡፡
ፋርቱን በሶማሊያ መንግሥት ጦር የተያዘችው ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር እንደሆነ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
ሴትዮዋም የድርጀቱ አባል እና የፋይናንስ አንቀሳቃሽ ነበረች ተብሏል፡፡
ፍርድ ቤቱ የእስር ቅጣት ውሳኔውን ሲያስተላልፍባት ይሄን ሁሉ ከግምት አስገብቶ መሆኑ ታውቋል፡፡
ሌላኛው የሶማሊያ የIS ቡድን ቅርንጫፍ ከፍተኛ መሪ ቢላል አል ሱዳኒ ሰሞኑን የአሜሪካ ልዩ ሀይል ወታደሮች በሰሜናዊ ምስራቅ የአገሪቱ ክፍል ባካሄዱት ዘመቻ መገደሉን ዘገባው አስታውሷል፡፡
የኔነህ ከበደ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments