top of page

ጥር 23፣ 2015- የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንሲስ ለታላቅ ሃይማኖታዊ ተልዕኮ ዛሬ ኮንጎ ኪንሻሳ ይገባሉ ተባለ


የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንሲስ ለታላቅ ሃይማኖታዊ ተልዕኮ ዛሬ ኮንጎ ኪንሻሳ ይገባሉ ተባለ፡፡


አባ ፍራንሲስ በነገው ዕለት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታዮች ሃይማኖታዊ መልዕክቶችን እንደሚያስተላልፉ ቫቲካን ኒውስ ፅፏል፡፡


ታላቅ የፀሎት ሥነ-ሥርዓት እንደሚከናወንም ታውቋል፡፡


በዚህም የተነሳ የአገሪቱ መንግስት የነገውን እለት ስራ የማይኖርበት ቀን አድርጎታል፡፡


ትምህርት ቤቶችም ዝግ ይሆናሉ ተብሏል፡፡


አባ ፍራንሲስ የኮንጎ ኪንሻሳ ጉብኝታቸው እንዳጠናቀቁ ወደ ደቡብ ሱዳን እንደሚያመሩ ዘገባው አስታውሷል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page