ጥር 22 2017 - አቶ ብርሃኑ አዴሎ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ
- sheger1021fm
- Jan 30
- 1 min read
አቶ ብርሃኑ አዴሎ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ፡፡
አቶ ብርሃኑ አዴሎ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ሆነው በምክር ቤቱ ተሹመዋል።
ቃል መሃላም ፈጽመዋል፡፡
አቶ ብርሃኑ የኢሰመኮ ኮሚሽነር የሆኑት ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር የስራ ዘመናቸው ያበቃውን ዶ/ር ዳንኤል በቀለን በመተካት ነው።

ከዶ/ር ዳንኤል የሃላፊነት ጊዜ ማብቃት ብኋል ላለፉት አምስት ወራት ኢሰመኮን በተጠባባቂነት የመሩት ራኬብ መሰለ ናቸው።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው የተሸሙት አቶ ብርሃኑ አዴሎ
የቀድሞው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ነበሩ፡፡
የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተርነት ሆነው መስራታቸውንም የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
Comments