top of page

ጥር 22፣ 2015- የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ ለዩክሬይን ምንም ዓይነት የጦር ጄት አንሰጥም አሉየጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ ለዩክሬይን ምንም ዓይነት የጦር ጄት አንሰጥም አሉ፡፡


ጀርመን ባለፈው ሳምንት ለዩክሬይን 14 ሊዮፓርድ 2 ታንኮችን ለመስጠት ቃል መግባቷን ኒውስ 18 አስታውሷል፡፡


አሜሪካም ለዩክሬይን 31 አብራምስ ታንኮችን እሰጥሻለሁ ብላታለች፡፡


በዚህ የተበረታቱት የዩክሬይን ሹሞች አሁን ደግሞ ምዕራባዊያኑ ዘመን አፈራሽ የጦር አውሮፕላኖችን እንዲያቀርቡላቸው ለመጠየቅ አላረፈዱም፡፡


የጀርመኑ መራሄ መንግስት ግን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በአሁኑ ወቅት ከሩሲያ ጋር በጦርነት ላይ አይደለም ብለዋል፡፡


በዚህም የተነሳ አገራቸው ጀርመን ለዩክሬይን የጦር ጄቶችን በጭራሽ አትሰጥም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


ከሩሲያ ጋር በጦርነት ላይ ያለችው ዩክሬይን የኔቶ አባል አይደለችም፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comentarios


bottom of page