
ስዊድን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /ኔቶ/ አባል የመሆን ጥረቷን ለጊዜው መግታቷን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቶቢያስ ቢልስቶርም ተናገሩ፡፡
ስዊድን ነባር የኔቶ አባል ከሆነችው ቱርክ ጋር ቅራኔዋ እየተባባሰ መምጣቱ የቃል ኪዳን ድርጅቱ አባል የመሆን ጥረቷን ለጊዜው እንድትገታው ማስገደዱን ቢል ስቶርም ተናግረዋል፡፡
ስዊድን እና ፊንላንድ የኔቶ አባላት ለመሆን በጣምራ ማመልከቻ ያቀረቡት ባለፈው አመት ነው፡፡
ሁለቱ አገሮች የኔቶ አባላት ለመሆን በጦር ቃል ኪዳን ድርጅቱ 30ውም አባል አገሮች መደገፍ ይኖርባቸዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት የቱርኩ ፕሬዘዳንት ሪቺፕ ታይፕ ኤርዶአን ስዊድን በጭራሽ ድጋፋችንን አትጠብቅ ማለታቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡
የስዊድኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጉዳዩን ዳግም ለማንቀሳቀስ ትንሽ እንጠብቃለን ማለታቸውን CGTN ፅፏል፡፡
የኔነህ ከበደ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comentarios