top of page

ጥር 21 2017 - አዋሽ ባንክ ሲያካሂድ የነበረውን የ2ኛው ዙር የስራ ፈጠራ ውድድር የማጠቃለያ መርኃ-ግብር አካሄደ

አዋሽ ባንክ ለስራ ፈጣሪዎች የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ ሲያካሂድ የነበረውን የ2ኛው ዙር የ “ታታሪዎቹ” የስራ ፈጠራ ውድድር የማጠቃለያ መርኃ-ግብር አካሄደ።


በብድር ማስያዣ እጥረት እና በተለያዩ ምክንያቶች የብድር ተጠቃሚ ያልሆኑ የስራ ፈጠራ ሀሳብ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸውን ስለታዘብኩ "ታታሪዎቹ" በሚል ስያሜ የስራ ፈጠራ ውድድር ፕሮጀክት አሰናድቼ ወደ ትግበራና ገብቻለሁ ብሏል።

በሁለተኛው ምዕራፍ የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ 5 ሺህ ተወዳዳሪዎች የተሳተፉበት መሆኑን ሰምተናል።


ከነዚህ የወዳዳሪዎች መላከልም አዳዲስ እና ችግር ፈች የሆኑ የስራ ሀሳብ ያላቸው ሰዎች በዳኞች ውሳኔ መሰረት መመረጣቸውን የሚናገሩት የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው ከ1 እስከ 5ኛ ደረጃ ለወጡ ተወዳዳሪዎች ከ200 ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ብለዋል።


በተጨማሪም ፕሮጀክታቸውን ወደ መሬት ለሚያወርዱበት እና ወደ ስራ ለሚገቡበት እስከ 5 ሚሊዮን ብር ብድር ያለዋስትና እንደ የፕሮጀክታቸው ሁኔታ ይመቻችላቸዋል ተብሏል፡፡


ፋሲካ ሙሉወርቅ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page