top of page

ጥር  21፣2016 - የድሬዳዋና የሐረር ከተሞች የ 5ጂ የሞባይል አገልግሎት ማግኘታቸው ተሰማ

ኢትዮ ቴሌኮም በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ በድሬዳዊ ፣በሐረር እና ሐሮማያ ከተሞች በሚገኙ  አካባቢዎች አገልግሎቱን አስጀምሯል።

 

ኢትዮ ቴሌኮም የአምስተኛው ትውልድ የሞባይል አገልግሎት ለተለያዩ ከተሞች በብርቱ እያቀበለ እንደሆነ ተናግሯል።

 

በድሬዳዋ ከተማ 5ጂ ያገኙት አካባቢዎች  ሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ አሸዋ ገበያ፣ ከዚራ ቴሌ፣ ቢ-ካፒታል ሆቴል፣ በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ በተስፋ ሆቴል እና የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ናቸው ።

 

በሐረርና ሀሮማያ ከተሞች ደግሞ በራስ መኮንን ትምህርት ቤት፣ በአራተኛ፣ በጀጎል እና ራስ ሆቴል/አጂፕ አካባቢዎች የ5ጂ አገልግሎት አግኝተዋል።

 

አምስተኛው ትውልድ ወደ ቢዝነስ መግባቱ ብዙ ነገርን ያቀላል ተብሏል።

 

5G  ምርት እንዲጨምር  የአሠራር ቅልጥፍና እንዲልቅ ፣ ቢዝነስና ንግድ በዲጂታል እንዲሰምር በብርቱ እንደሚያግዝ ተሰምቷል።

 

ይህ ፈጣን አገልግሎት  ለዘመናዊ ቤት (Smart home)  የጤና አገልግሎት እና የሆስፒታል አስተዳደር፣ ለስማርት ግብርና፣ ትምህርት፣ ማዕድን፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ኤርፖርት ፣ ትራንስፖርት፣ ለብሮድካስቲንግና ለሌላውም ሥራን እንደሚያቀላጥፍ የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።



የ5ጂ የሞባይል ኔትወርክ ዳታ የማስተላለፍ መዘግየትን እጅግ በላቀ ሁኔታ በመቀነስ (Ultra-low latency) ወደ 1ሚሊ በሰከንድ የሚያደርስ ነው።

 

በአንድ ካሬ ኪሎ ሜትር ውስጥ እስከ 1 ሚሊዮን የሚደርሱ በርካታ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን እርስ በርሳቸው ለማገናኘት የሚያስችል ዓለሚቱ የደረሰችበት  ዘመናዊ የገመድ አልባ ኔትወርክ ቴክኖሎጂ መሆኑ ተነግሮለታል፡

 

አገልግሎቱ በይፉ በሁለቱም ከተሞች ሲጀመር የየከተማው ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተው ነበር።

 

 

ተህቦ ንጉሴ

 


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 


 

 

 

Коментари


bottom of page