ከዛሬ 89 ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ የተሰራችው እና "ፀሐይ" በመባል የምትታወቀውን አውሮፕላን ኢትዮጵያ ተረከበች፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “ፀሐይ” በመባል የምትታወቀው እና በ1927 ዓ.ም በኢትዮጵያ የተሰራችውን አውሮፕላን ከጣሊያን መንግስት በይፋ ተረክበናል ብለዋል፡፡
የአውሮፕላኗን የማስመለስ ስራን በማገዛቸው የጣሊያኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆአርጂያ ሜሎኔን አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡
ፀሐይ በመባል የምትታወቀው አውሮፕላን የተሰራችው በአዲስ አበባ ጃንሜዳ በ1927 ዓ.ም ነው።
ስለ አውሮፕላኗ እና ስለ ኢትዮጵያ አቪየሽን አጀማመር መፃፍ የፃፉት ካፒቴን ዘለዓለም አንዳርጌ አውሮፕላኗ በኢትዮጵያ እና ዌበር በሚባል ጀርመናዊ አብራሪ እና ኢንጂነር መሰራቷን ነግረውን ነበር።
አውሮፕላኗ ስያሜዋንን ያገኘችውም በአፄ ኃይለስላሴን ልጅ ልዕልት ፀሐይ ነው።
ፀሐይ ሁለት መቀመጫ እና ሁለት የፊት ጎማ እንዲሁም ከኋላ መንሸራተቻ ብረት የተገጠመላት አውሮፕላን ነች።
አውሮፕላኗ በጣሊያንን ወረራ ወቅት ከሀገር መውጣቷ እና በጣሊያን ሀገር የተለያዩ ሙዚየሞች ወስጥ መቀመጧን ፣ የአሁን ቀለሟም ስትሰራ እንደነበረው እንዳልሆነ ካፒቴን ዘለዓለም ነግረውናል።
ለሀገር ቤት እንድትበቃ ብርቱ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩት ካፒቴን ዘለዓለም ለመፃህፍ ዝግጅትም ሆነ የምትመለስበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ከአጣሊያን የተለያዩ ሀላፊዎች ጋር ሲነጋገሩም ነበር።
በዛሬው እለትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ "ፀሐይ አውሮፕላንን ከጣልያን መንግሥት በይፋ መረከባችንን የምናከብርበት ቀን በመሆኑ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ታላቅ የኩራት ቀን ነው" ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላለፈው አንድ ዓመት ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኔ ጋር አውሮፕላኗ ወደ ኢትዮጵያ ስለምመለስበት ሁኔታ ትልቅ ጥረት እና ሰፊ ንግግር ሲያደርጉ ቆይተዋል ሲል ፅ/ቤታቸው ተናግሯል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments