top of page

ጥር 20፣ 2015- አሜሪካ የጦር መሳሪያ ገበያው ደርቶላታል ተባለ


አሜሪካ የጦር መሳሪያ ገበያው ደርቶላታል ተባለ፡፡


ከወር ገደማ በፊት በተጠናቀቀው ዓመት የአሜሪካ የጦር መሳሪያ ንግድ በ49 በመቶ ማደጉን CGTN ፅፏል፡፡


ዘገባው በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መረጃ ላይ የተንተራሰ መሆኑ ታውቋል፡፡


ለአሜሪካ የጦር መሳሪያ ገበያ ማደጉ የዩክሬይኑ ጦርነት በዋና ምክንያትነት ቀርቧል፡፡


ንፅፅሩ የተሰራው ከቀዳሚው አመት ጋር ተመሳክሮ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡


አሜሪካ በመንግስት ለመንግስት የመከላከያ ውለታ በአመቱ የ154 ቢሊዮን ዶላር የዋጋ ግምት ያላቸውን የጦር መሳሪያዎች እንደቸበቸበች ዘገባው አስታውሷል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page