
በኢራን አንድ ታጣቂ በአዘርባጃን ኤምባሲ ላይ በከፈተው ጥቃት የጥበቃ ሀላፊውን መግደሉ ተሰማ፡፡
በጥቃቱ ሁለት የጥበቃ ባልደረቦች ደግሞ አካላዊ ጉዳት እንደገጠማቸው ዘ ቴሌግራፍ ፅፏል፡፡
ጥቃት አድራሹ ወዲያውኑ መያዙ ታውቋል፡፡
አዘርባጃን እና በርካታ አገሮች ጥቃቱ የሽብር ጥቃት ነው በሚል ማውገዛቸው ተሰምቷል፡፡
የኢራን ሹሞች ግን ጥቃቱ የተፈፀመው በቤተሰብ ችግር ምክንያት ነው ብለዋል፡፡
ጥቃቱን በብርቱ ካወገዙ እና ከኮነኑት መካከል እስራኤል እና ሳውዲ አረቢያ እንደሚገኙበት በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
የኔነህ ከበደ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments