top of page

ጥር 2፣2016 - የኢትዮጵያን ሲቪል ማህበረሰብን ያግዛል የተባለ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ ነውም ተብሎለታል።


ይህ የተባለው በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ ሊከወን የታሰበው ፕሮግራም ይፋ በሆነበት ወቅት ነው።


ፕሮግራሙን በዋናነት የሚመራው ዌልት ሀንገር ሂልፌ(Welt Hunger Hilfe) የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት መሆኑን ሲነገር ሰምተናል።


መርሃ ግብሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የተለያዩ የፖሊሲ ውይይት ላይ እንዲሰማሩ፣ ሀገራዊ፣ ክልላዊ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ተጽእኖ የማድረግ አቅማቸውን እንዲያበረቱ ለማድረግ የሚረዳ ነው ተብሏል።


ለአምስት ዓመታት ይቆያል የተባለው ይህ ፕሮጀክት 90 በመቶ የሚሆነው በጀት በአውሮፓ ህብረት የሚሸፈን ሲሆን የተቀረው 10 በመቶው ደግሞ በ Welt Hunger Hilfe (WHH) በኩል የሚሟላ መሆኑን ሰምተናል።


በአዲስ አበባ፣ በአፋር፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ እና በአማራ ክልል የሚተገበረው ይህ ፕሮግራም ከፖሊሲ ጋር በተገናኘ የሚከወኑ ስራዎችም ይኖሩታል ተብሏል።


በተጨማሪም ፕሮግራሙ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን የቴክኒካል እና የገንዘብ ድጋፍ ላይ ለማገዝ ታሳቢ አድረጎ የሚሰራ መሆኑን ሰምተናል።


ለፕሮጀክቱ ከተበጀተው አጠቃላይ 6.52 ሚሊዮን ዮሮ 4 ሚሊዮኝ ዩሮው ለሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚውል ነው ተብሏል።


ፋሲካ ሙሉወርቅ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



コメント


bottom of page