top of page

ጥር 2፣2016 - የመሬት አስተደር ችግር ባለመፈታቱ የመልካም አስተዳደር መንስኤ ሆኖዋል ሲል የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ተናገረ


የመሬት አስተደር ችግር ባለመፈታቱ የመልካም አስተዳደር መንስኤ ሆኖዋል ሲል የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ተናገረ፡፡


የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ይሄን የተናገረው ዛሬ የመሬት አስተዳደር ችግሮችን ያመላከተ የመጀመሪያ ምክረ ሀሳብ ሰነድ በኢትዮጵያ የመሬት አስተዳደር ባለሞያዎች ማህበር ለውይይት በቀረበበት ወቅት ነው፡፡


የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ድኤታ ፋንታ ደጀን የመሬት አስተዳደር ችግር ሳይፈታ ለበርካታ ዓመታት ዘልቋል ብለዋል፡፡


በመሬት አስተዳደር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች ከመቀነስ ይልቅ እየበዙ መምጣቸውን ሚኒስትር ድኤታው ሲናገሩ ሰምተናል፡፡


የኢትዮጵያ የመሬት አስተዳደር ባለሞያዎች ማህበር ፕሬዘዳንት ዶ/ር አቻሜለህ ጋሹ መሬት ለሀገር እድገት ዋና ቁልፍ መሆኑን አንስተው በአግባቡ ማስተዳደር ባለመቻሉ የግጭቶች ምክንያት ሆኗል ብለዋል፡፡


መሬትን ስራዬ ብሎ የሚያስተዳድረው አንድ ተቋም ባለመኖሩ ህገወጥ የመሬት ወረራ ያለአግባብ በልማት ሰበብ ነዋሪዎችን ማንሳት፣ ሲነሱም ያለ በቂ ካሣ እንዲነሱ መደረግ፣ የመኖሪያ ቤት እጥረትና መሰል ችግሮች በስፋት ይስተዋላሉ ብለዋል፡፡


ለዚህም መፍትሄ ዘመናዊ የመሬት አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት ነው ሲባል ሰምተናል ብለዋል፡፡



ያሬድ እንዳሻው



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page