ጥር 19፣2017 - ከነገ ጀምሮ ከፊጋ - ወደ ሳፋሪ በሁለቱም አቅጣጫች መንገዶች ላልተወሰኑ ቀናት ዝግ እንደሚሆኑ ተነገረ፡፡
- sheger1021fm
- Jan 27
- 1 min read
ከነገ ጀምሮ ከፊጋ - ወደ ሳፋሪ በሁለቱም አቅጣጫች መንገዶች ላልተወሰኑ ቀናት ዝግ እንደሚሆኑ ተነገረ፡፡
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ከነገ ጥር 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከፊጋ - ወደ ሳፋሪ እንዲሁም ከሳፋሪ -ወደ ፊጋ የሁለቱም አቅጣጫ መንገዶቹ ላልተወሰኑ ቀናት ዝግ እንደሚሆን ተናግሯል፡፡
በአዲስ አበባ በ2ኛው ዙር ከሚለሙት የኮሪደር መስመሮች መካከል የሰሚት- ጎሮ መንገድ አንደኛው መሆኑ አስታውሶ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የሲ ኤም ሲ- ፔፕሲ - ጎሮ - መንገድ ልዩ ቦታው ሳፋሪ መብራት አካባቢ ብሪቲሽ ትምህርት ቤት አጠገብ የመንገድ ቆረጣ ይከወናል ተብሏል።
በዚህም መሰረት ከነገ ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናት ከፊጋ - ወደ ሳፋሪ እንዲሁም ከሳፋሪ -ወደ ፊጋ የሁለቱም አቅጣጫ መንገዶቹ ዝግ እንደሚሆኑ ባለስልጣን መ/ቤቱ ተናግሯል።
የመንገዱ ተጠቃሚ አሽከርከሪዎች ይህንን አውቀው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ሲል የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አሳስቧል፡፡
Comments