top of page

ጥር 19 2017 - ትላልቆቹ የግብርና ምርምር እና የእንስሳት ብዜት ማዕከላት የመሬት ይዞታቸውን በከተማ አስተዳደሮች እና በክልሎች እየተወሰደባቸው ነው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Jan 27
  • 1 min read

ትላልቆቹ የግብርና ምርምር እና የእንስሳት ብዜት ማዕከላት የመሬት ይዞታቸውን በከተማ አስተዳደሮች እና በክልሎች እየተወሰደባቸው ነው ተባለ፡፡


የመሬት ይዞታቸው ተወስዶባቸዋል ከተባሉት ትላልቅ ማዕከላት መካከል የሆለታ፣ የጅማ፣ የቁልምሳ እና የቢሾፍቱ የግብርና እና የእንስሳት እርባታ ማዕከላት እንደሚገኙበት ተነግሯል፡፡


ከእነዚህ ተቋማት በአጠቃላይ 312 ሔክታር መሬት በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች ተነጥቀዋል ተብሏል፡፡


በዚህም የግብርና ምርምር እና የእንስሳት ብዜት ማዕከላት ህልውናቸው አደጋ ላይ እንደሆነም ተነስቷል፡፡

ማዕከላቱ የመሬት ይዞታቸው ባለመረጋገጡም ለግበርናው ዘርፍ ማበርከት የሚገባቸውን ከፍተኛ ሚና እያደናቀፈባቸው ነው ተብሏል፡፡


በተጨማሪም በክልሎች ጥያቄ መሰረት የተቋቋሙ የምርምር ማዕከላት ላይም የተለያዩ ችግሮች አንደሚታዩባቸው ተጠቁሟል፡፡


ከእነዚም መካካልም የወረ ኢሉ የግበርና ምርምር ማዕከል የመሰረት ድንጋይ ቢቀመጥለትም እስካሁን ግንባታው አልተጀመረም ተብሏል፡፡


ይህ የተባለው የግብርና ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የ6 ወር ዕቅድ አፈጻፀም ሪፖርት ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡


ቋሚ ኮሚቴው ይህንን ማረጋገጥ የቻልኩት በቅርቡ የክትትልና የቁጥጥር ምልከታ ባደረኩበት ወቅት እንዲሁም ከማዕከላቱ ባገኘሁት መረጃ ነው ብሏል፡፡


የግብርና ሚኒስቴር፣ የምርምር ማዕከላቱ ይዞታቸውን እንዲረጋገጥ እንዲሰራም በቋሚ ኮሚቴው ተጠይቋል፡፡


ማንያዘዋል ጌታሁን

コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page