2014 የትምህርት ዘመን 12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች መካከል 1,161 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም ተባለ፡፡
በሌላ በኩል 7 ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸው ሁሉም ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል፡፡
ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ያሳለፉት ትምህርት ቤቶች ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት፣ ኦዳ ልዩ አዳሪ ት/ቤት፣ ባህርዳር ስቴም ት/ቤት፣ ወላይታ ሊቃ ት/ቤት፣ የጎንደር ማህበረሰብ አቀፍ ትምህርት ቤት እና ከግል ለባዊ ት/ቤት መሆናቸውን ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡
የ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች ከ50 በመቶ በላይ ያመጡት 3.3 በመቶ ብቻ መሆናቸው ተናግሯል፡፡
ፈተናውን በትክክል ከወሰዱት 896,520 ተማሪዎች ውስጥ ከግማሽ ወይንም ከ50 በመቶ በላይ ያመጡት፤ 29,909 መሆናቸውን ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስረድተዋል።
በዚህም መሰረት ከግማሽ በላይ ያመጡት 29,909 ተማሪዎች በቀጥታ ወደ ዩኒቨርስቲ ገብተው የአንደኛ ዓመት ተማሪ ይሆናሉ።
ወደ ዩኒቨርስቲ የሚያስገባቸወን ውጤት ያላመጡ ተማሪዎችን በተመለከት የትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አሰራር ለመከተል ማቀዱን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።
ተመስገን አባተ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments