top of page

ጥር 18፣ 2015- ከሁለት ዓመት በኋላ ኢትዮጵያን ከአለም 5 ዋነኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻዎች አንዷ ማድረግን ያለመ ፎረም ዛሬ በአዲስ አበባ ተከፈተ

  • sheger1021fm
  • Jan 26, 2023
  • 1 min read


ከሁለት ዓመት በኋላ ኢትዮጵያን ከአለም 5 ዋነኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻዎች አንዷ ማድረግን ያለመ ፎረም ዛሬ በአዲስ አበባ ተከፈተ።


ፎረሙ ኢትዮጵያን ከአለም 5 ዋነኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻዎች አንዷ በማድረግ 2 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት የመሳብ ግብ እንዳለው ተነግሯል።


በኢትዮጵያ ፌዴራል መሬት ባንክ ልማት ኮርፖሬሽን የተሰናዳው ይህ መድረክ Invest Origins 2023 የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።


በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ የዘርፉ ባለሞያዎች ዛሬ እና ነገ እንደሚመክሩ ተጠቅሷል።


ባለሃብቶችን እና ሌሎች የኢኮኖሚ ተዋናዮችን ለመሳብ ለኢትዮጵያ ጥሩ አጋጣሚ እንደሆነም በሳይንስ ሙዚየም በተከፈተው ፎረም ላይ ሲነገር ሠምተናል።


በኢንተርኔት መላም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ፎረሙን እየተከታተሉት እንደሚገኙ ተነግሯል።


ንጋቱ ረጋሳ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page