top of page

ጥር 18፣ 2015የአሜሪካው ገናና የአውሮፕላን አምራች ቦይንግ ኩባንያ ክስ ሊመሰረትበት ነው ተባለ


ጥር 18፣ 2015


የአሜሪካው ገናና የአውሮፕላን አምራች ቦይንግ ኩባንያ ክስ ሊመሰረትበት ነው ተባለ፡፡


ጉዳዩ ከ4 ዓመታት በፊት በወራት ልዩነት የመከስከስ አደጋ ከገጠማቸው የኢንዶኔዥያው ላየን ኤር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማክስ 8 አውሮፕላኖች ጋር የተያያዘ እንደሆነ ሎው 360 ፅፏል፡፡


በሁለቱም አደጋዎች 346 ሰዎች ማለቃቸው ለትውስታ ተጠቅሷል፡፡


አደጋዎቹ የደረሱት አውሮፕላኑ በነበረበት የአውቶማቲክ የበረራ ሂደት መቆጣጠሪያ M ካስ ምክንያት እንደነበር ተረጋግጧል፡፡


በአደጋዎቹ ምክንያት ማክስ 8 አውሮፕላን ከአመት በላይ ለሆነ ጊዜ በአለም ዙሪያ ከበረራ ውጭ ተደርጎ ቆይቷል፡፡


ቀደም ሲል ቦይንግ ለቅጣት እና ለካሣ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል መስማማቱን ዘገባው አስታውሷል፡፡


አሁን ደግሞ የአደጋው ሰለባዎች ቤተሰቦች ቦይንግ በአደጋዎቹ ህጋዊ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል በማለት ፍርድ ቤት ሊገትሩት መሆኑ ተሰምቷል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Comments


bottom of page