top of page

ጥር 17፣2016 - አቶ ደመቀ መኮንን ከብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትነት ለቀቁ

አቶ ደመቀ መኮንን ከብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትነት ለቀቁ፡፡


የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ የፓርቲውን የአመራር የመተካካት መርህንና የአሰራር ስርዓት በመከተል ዛሬ ባካሄደው ማጠቃለያ ስብሰባ አቶ ደመቀ መኮንንን በሙሉ ድምፅ በክብር ሸኝቷል ተብሏል፡፡


በአቶ ደመቀ ምትክም የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ አባል የነበሩት አቶ ተመስገን ጥሩነህን ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው በአብላጫ ድምጽ መመረጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።


ብልጽግና ፓርቲ ሁለት ምክትል ፕሬዝዳንቶች ሲኖሩት አንደኛው አቶ አደም ፋራህ ናቸው፡፡


ሌላኛው ዛሬ በአቶ ተመስገን ጥሩነህ የተተኩት አቶ ደመቀ መኮንን ነበሩ፡፡የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…Comments


bottom of page