የካሜሩን መንግስት ማንኛውም የውጭ ሀይል እንዲሸመግለን አንሻም አለ፡፡
በቅርቡ ካናዳ የካሜሩን ተፋላሚዎችን ለማደራደር ተሰናድቻለሁ ፤ ለዚህም የተደራዳሪዎቹን ይሁንታ አግኝቻለሁ የሚል መግለጫ አውጥታ እንደነበር ዘ ግሎብ ሜይል አስታውሷል፡፡
የካሜሩን መንግስት የውጭ ሀይሎችን ሽምግልና እና አደራዳሪነት አንሻም ማለቱ ካናዳን ኩም አድርጓታል፡፡
የካሜሩን መንግስት ጦር በአገሪቱ ሰሜን እና ደቡብ ምዕራብ ግዛቶች ከሚገኙ የመገንጠል አቀንቃኞች ጋር ሲዋጋ 7 አመታትን አስቆጥሯል፡፡
የውጭ ሀይሎችን አደራዳሪነት በጭራሽ አንቀበልም ያለው የካሜሩን መንግስት ጉዳዩ የውስጥ ችግራችን ስለሆነ ለእኛው ተውልን ማለቱ ተሰምቷል፡፡
የኔነህ ከበደ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments