ጥር 16 2017 - ‘’ከመስከረም አጋማሽ እስከ ታህሳስ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ብቻ 213 ሰዎች ከፍርድ ውጪ ተገድለዋል’’ ኢሰመኮ
- sheger1021fm
- Jan 24
- 1 min read
በአማራ ክልል በሶስት ወራት ውስጥ ብቻ 129 ንጹሃን ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ፡፡
በኦሮሚያ ክልል ደግሞ 84 ሰዎች መገደላቸው ኮሚሽኑ ጠቅሷል፡፡
ከመስከረም አጋማሽ 2017 ዓ.ም እስከ ታህሳስ ወር 2017 ዓ.ም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ብቻ 213 ሰዎች ከፍርድ ውጪ መገደላቸውን ኮሚሽኑ አስረድቷል፡፡

ግድያዎቹን የፈፀሟቸውም የመንግስት የፀጥታ ሀይች፣ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን በተለምዶ (ፋኖ) እና በኦሮሚያ ክልል የሚቀሳቀሰው በተለምዶ (ሸኔ) መሆናቸውን ኮሚሽኑ በሪፖቱ አስፍሯል፡፡
ለንጹሃኑ ግድያ ምክንያት የሆነው በታጣቂዎቹ በኩል መንግስትን ትደግፋላችሁ፣ በመግስት የፀጥታ ሀይች በኩል ደግሞ ታጣቂዎቹን ትደግፋላችሁ በሚል እንደሆነ ኮሚሽኑ የዓይን እማኞችን እና የተጎጂ ቤተሰቦች በማነጋገር ያወጣው ሪፖርት ያስረዳል፡፡
ኮሚሽኑ በሪፖርቱ የዘፈቀደ ፣ ጅምላና የተራዘመ እስራትና የተፋጠነ ፍትህ እጦት ያጋጠማቸውን ፣ አስድዶ መወሰር ፣ እገታ እና ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ ታስረው የቆዩ ሰዎችን ፣ የተፈናቀሉ ሰዎችን እንዲሁም የንብረት መውደምን አካቷል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
Comments