top of page

ጥር 16 2017 - አዋኪ ናቸው የተባሉ፤ እንደ መጠጥ ቤቶች፣ ቁማር ቤቶች እና ሌሎች ከ1,900 በላይ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዷል ተባለ

በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ ባሉ ትምህርት ቤቶች ዙሪያ አዋኪ ናቸው የተባሉ፤ እንደ መጠጥ ቤቶች፣ ቁማር ቤቶች እና ሌሎች ከ1,900 በላይ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዷል ተባለ፡፡


እነዚህ ከ1,900 በላዩ የንግድ ተቋማት በ #ትምህርት_ቤቶች ዙሪያ በ500 ሜትር ራዲየስ ላይ የሚገኙ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ከትምህርት ቤቶቹ ከ200 - 500 ሜትር ራዲየስ ላይ ያሉ 936 የንግድ ተቋማት መታሸጋቸውን ሰምተናል፡፡

ይህንን የሰማነው ከከተማዋ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ነው።


በትምህርት ቤቶች ዙሪያ የነበሩ እና አገልግሎት መስጠት ያቆሙት እነዚህ #የንግድ_ተቋማት ተለዋጭ ቦታ ተሰጥቷቸው እንዲሰሩ እየተደረገ ነው የተባለ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ በዚያው ቦታ ላይ ዘርፍ ቀይረው እንዲሰሩ መደረጉ ተነግሯል።


በተጨማሪም ሸቀጦች ላይ ያለ አግባብ ዋጋ በጨመሩ፣ በህገወጥ መንገድ ምርት ያከማቹ ነጋዴዎችም ተገኝተው ቅጣት ተጥሎባቸዋል ያለው ቢሮው በዚህም በበጀት ዓመቱ 2,000 የሚደርሱትን ቀጥቻለሁ ብሏል።


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page