በጤና አገልግሎት ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን በመፍታትና የተሻለ አሰራር በመፍጠር ማህበረሰቡ በአገልግሎቱ ላይ እምነት ሊኖረው ማድረግ ያስፈልጋል ተባለ፡፡
ለዚህም ያግዛል የተባለ የጤናው ዘርፍ የማህበራዊ ተጠያቂነት ስትራቴጂ ይፋ ተደርጓል፡፡
ስትራቴጂው በጤና አገልግሎት አሰጣጡ ላይ ከተቋማት ጀምሮ ባለሙያዎችና አስተዳደር ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችም በመመርመር መፍትሄ ለመስጠት ከማህበረሰቡ ጋር በጋራ የሚሠራበት ነው ተብሏል።
በጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በተመለከተ ባለፈው ዓመት 2016 እንኳን በቁጥር የተሻለ አገልግሎት የተሰጠበት ነው ያሉት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ ነገር ግን አሁንም የሚቀሩ በርካታ መሻሻል ያለባቸው ስራዎች በመኖራቸው ስትራቴጂው መሰናዳቱን ተናግረዋል፡፡
በተለያዩ የጤና አገልግሎቶች ላይ የታዩ ለውጦችን የጠቀሱት ሚኒስትሯ ነገር ግን አሁንም ኢትዮጵያ እየተፈተነችበት ባለው እንደ ግጭትና ወረርሽኞች ምክንያት በጤና ተቋማትና አገልግሎቱ ላይ የደረሱትን ችግሮች ማስተካከል ላይ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ለምሳሌ የእናቶች ሞት፣ የጨቅላ ህፃናት ሞት ምን ያህ ቀንሷል? የሚለውን መመለስ የመድኃኒታ አቅርቦት ከውጪ ብቻ የሚመጡ የነበሩትን በሀገር ውስጥ ተኪ ነገሮች በመስራት የህክምና አገልግሎቱን ለህዝቡ የማድረስ አቅም ጨምረናል ሲሉ የተናገሩት ሚኒስትሯ ግን አሁንም ደግሞ ሀገገሪቱ በተለይ ደግሞ በባለፉት ዓመታት በተለይ ኮቪድ፣ እንዲሁም ደግሞ የአየር ንብረት ለውጥ ግጭቶች ብዙ ነገሮች ደግሞ የጤና ተቋማትና የጤና አገልግሎት ላይ ብዙ ጥያቄዎች የፈጠሩበት አመት ነበር ብለዋል፡፡
እስትራቴጂው የጤና አገልግሎት ተጠቃሚዎች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች በአግባቡ በመመለስ ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ እንደሆነና በተለያዩ መመዘኛዎች ልክ የተሰናዳ መሆኑን የጠቀሱት ደግሞ በጤና ሚኒስቴር የስራ አመራር ዋና አስፈፃሚ የሆኑት ዶክተር አስናቀ ዋቅጅራ ናቸው፡፡
የጤና ዘርፍ የማህበራዊ ተጠያቂነት ስትራቴጂ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚዎች የሚያነሷቸውን ቅሬታዎች በማሰባሰብ ምላሽ መስጠት እንዲሁም ፖሊሲዎችና አገልግሎት ሰጪዎች ተጠያቂ የሚደረጉበት እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ሙሉ ዘገባን ያድምጡ…. https://tinyurl.com/mr47b9sh
ምህረት ስዩም
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5rs
Comments