ጥር 16 2017 - በአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት በእፅ አዘዋዋሪዎች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር እንዲጠብቅ ተጠየቀ።
- sheger1021fm
- Jan 24
- 2 min read
በአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት በእፅ አዘዋዋሪዎች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር እንዲጠብቅ ተጠየቀ።
በተለይ መነሻቸው ከደቡብ አሜሪካ ያደረጉ መንገደኞች ላይ ቁጥጥሩ እንዲበረታ ተጠይቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በበኩሉ ችግሩ ያለው ከመንገደኞች መነሻ ሀገር (በአብዛኛው እንደ ብራዚል ያሉ የደቡብ አሜሪካ ሀገሮች) ባለ የቁጥጥር ማነስ እንጂ በእኔ ምክንያት አይደለም ብሏል።
አሁን አሁን የአደገኛ እፅ ዝውውር መልኩን እየቀያየረ ይገኛል።
እፅ አዘዋዋሪዎቹ ለውጥናቸው ማስፈፀሚያ እፁን ከላቲን አሜሪካም ሆነ ከናይጄሪያ ወደ ኤዢያ ወደ እነ ሆንግ ኮንግሀ፣ ቻይና፣ ሰሜን አሜሪካ፣ አውሮፓ ሀገሮች የሚያስተላልፋቸውን ሰዎች ይመለምላሉ፡፡
ጠቀም ያለ ዶላር እንደሚያስታቅፏቸው ይነግሯቸዋል፡፡

ተመልማዮቹ በአብዛኛው አፍሪካዊያን ናቸው፡፡
አስተላለፊዎቹም እፁን እንደ እቃ ጠቅልለው ፣ ሌላ እቃ አስመስለው በቦርሳቸው ይዘው ብቻ ሳይሆን በሆድ እቃቸው ይዘው ለማስተላለፍ ጥረት ያደርጋሉ፡፡
እጹን በአነስተኛ መጠን በላቲክ ይጠቀለል፣ አንዳንዴ እንደውም በኮንዶም ሁሉ እንደሚጠቀለል ሰምተናል፡፡
የተጠቀለለውን እፅ እንደ ቂቤ ያሉ ቅባቶችን፣ እንደ ኮካ ኮላ ያሉ መጠጦችን ለማለስለሻነት እየተጠቀሙ ይውጡታል፡፡
እነ ከኮይንን በሆዱ የያዘ እፅ አዘዋዋሪ ለሕይወቱ አደገኛ ፣ ቢያዝ እጣው መገደል ወይንም መታሰር መሆኑንን እያወቅም ይሁን ሳያውቅ አውሮፕላን ተሳፍሮ ይጓዛል፣ሀ ባህር አቋርጦ ለመጓዝ ይነሳል።
ምግብ እንዲመገብ አይፈቀድለትም፡፡
በዚህ መላ አደገኛ እፅ ለማስተላለፍ ከሚፈተኑ ኤርፖርቶችን መካከል አንደኛው የአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ነው፡፡
መቀመጫውን በሆንግ ኮንግ ያደረገውን Voice fore prisoners የተባለው ድርጅት በአደገኛ ዕፅ ዝውውር ምክንያት ለእስር የሚዳረጉ ሰዎችን ያግዛል፡፡
የድርጅቱ ሀላፊ ጆን ዋትርስፑን ሰሞኑንን አዲስ አበባ ላይ በሰጡት መግለጫ በአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት በእፅ አዘዋዋሪዎች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር እየጠበቀ መምጣቱን ተገንዝበናል ግን አሁን ስራዎች ይቀራል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ከደቡባዊ አፍሪካ ሀገሮች ተመልምለው አዲስ አበባ ከመጡ ብኋላ ኮኬይን በሆዳቸው ይዘው ወደ ሆንግ ኮንግ የሄዱና በዚያ የተያዙ ሰዎች ለአብነት አንስተዋል።

ከዚህ ቀደም ይህንን የእፅ ዝውውርን በተመለከተ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ላቀረብንላቸው ጥያቄ ችግሩ እያጋጠመ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መንገደኞችን ወደ አውሮፕላኑ ወይንም ከሌላ ሀገር ተቀብሎ ሲያሳፍር መፈተሸ ስለማይችል ችግሩ ከመነሻው ሀገር ያለ የተንዛዛ አሰራር እና ጥብቅ ፍተሻ ባለመኖሩ ነው፤ በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድን ስም መነሳት የለበትም ብለዋል።
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5rs
Comments