top of page

ጥር 16፣2016 - የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉዞ ትኬቶችን በሳፋሪኮም ኤም-ፔሳ በኩል መግዛት የሚያስችል ሰምምነት ተፈረመ

በሳፋሪኮም ኤም-ፔሳ በኩል የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉዞ ትኬቶችን መግዛት የሚያስችል ሰምምነት ተፈረመ፡፡


ስምምነቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ዋና ሀላፊ አቶ ለማ ያዴቻ እና የሳፋሪኮም ኤም-ፔሳ የዲጂታል ፋይናንስ ዋና ሃላፊ ፖውል ካቫቩ ተፈራርመውታል፡፡


በስምምነቱ መሰረት የሳፋሪኮም ኤም-ፔሳ ደንበኞች የጉዞ ትኬቶቻቸውን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሞባይል መተግበሪያ፣ ድረ-ገጽ ወይም በአየር መንገዱ አለም አቀፍ የጥሪ ማእከል በኩል እንዲገዙ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡


ይህም ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ቀልጣፋ እና አስተማማኝ ክፍያዎችን ለመፈጸም ያስችላል ተብሎለታል።


የሳፋሪኮም ኤም-ፒኤሳ ደንበኞች ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ አየር የጉዞ ትኬቶችን ፣ የበረራ ለይ ግዢዎችን፣ የሻንጣ ክፍያ እና ሌሎች ከፍያዎችን በቀላሉ ማከናወን ይችላሉ ተብሏል፡፡የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…bottom of page