top of page

ጥር  15፣2016 - ዎርልድ ቪዥን የንጹህ የመጠጥ ውሃ ግንባታ ለማጠናቀቅ የትራንስፎርመር እጥረት እንቅፋት ሆኖብኛል አለ

ዎርልድ ቪዥን በወላይታ ዞን 5 ወረዳዎች እያስገነባው ያለሁት  የንጹህ የመጠጥ ውሃ ግንባታ ለማጠናቀቅ የትራንስፎርመር እጥረት እንቅፋት ሆኖብኛል አለ።

 

ወርልድ ቪዥን በዞኑ በ5 ወረዳዎች 22 የውሃ ጉድጓዶችን የቆፈረ ሲሆን ከሁለቱ ጉድጓዶች በስተቀር ሌሎቹ ተሰርተው ወደ ስራ ገብተዋል ተብሏል።

 

ሁለቱ ጉድጒዶች ስራቸው ቢጠናቀቅም ትራንስፎርመር ባለመገኘቱ ጉድጓዶቹ ወደ ስራ አለመግባታቸው ተነግሯል።

 



ወርልድ ቪዥን ‘’ጌሻሮ ፕሮጀክት’’ በሚል በ5ቱ ወረዳዎች ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና የብልሀርዝያ እና የአንጀት ትላትል የመከላከል ስራ እየሰራ መሆኑን የፕሮጀክቱ ዳይሬክተር እንድርያስ ሸቤው ነግረውናል።

 

የንጽህ መጠጥ ውሃ ጉድጓዶቹ በኤሌክትሪክ እና በሶላር ሀይል አገልግሎት ያገኛሉ ተብሏል።

 

የጌሻሮ የውሃ ፕሮጀክት የአካባቢው ነዋሪዎች የውሃ መሸጥና የተለያዩ የስራ እድሎች ተፈጥሮላቸዋል መባሉን ሰምተናል።

 

ፕሮጀክቱ ላለፉት 5 ዓመታት ሲሰራ ነበር የተባለ ሲሆን አሁን ላይ እየተጠናቀቀ ነው ተብሏል፡፡

 

 

በረከት አካሉ

 

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

Comentários


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page