top of page

ጥር 13፣ 2017 - የቦሌ አራብሳ የአይሲቲ ፓርክ የመንገድ ግንባታ በተያዘው ዓመት ተጠናቆ ወደ ስራ ይገባል ተባለ

የቦሌ አራብሳ የአይሲቲ ፓርክ የመንገድ ግንባታ በተያዘው ዓመት ተጠናቆ ወደ ስራ ይገባል ተባለ፡፡


የግንባታ ሂደቱ 25 በመቶ የደረሰው ይህ የቦሌ አራብሳ የአይሲቲ ፓርክ መንገድ 1.4 ቢሊየን ብር ከመንግስት በኩል እንደተመደበለት ሰምተናል፡፡


መንገዱ 6 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 60 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡


ይህ መንገድ የቦሌ አራብሳ ነዋሪዎች ወደ አይሲቲ ፓርክ እንዲሁም ከቦሌ #ኤርፖርት ወደ ጎሮ የሚገናኝ በመሆኑ በአጭር ርቀት ወደ መሐል ከተማ የሚያገናኛቸው ነው ሲሉ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ነግረውናል፡፡


በአጠቃላይ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱን የአፈር ቆረጣ፣ የድሬኔጅ መስመር ዝርጋታ የድልድይ ግንባታ ስራዎች እየተከናወነ ነው ብለውናል፡፡


በተያያዘም #የአየር_ጤና ወለቴ መንገድ በኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ መዘግየት ምክንያት በታሰበለት ፍጥነት እየተከናወነ አይደለም ተብሏል፡፡


ችግሩን ለመፍታት ከተቋሙ ጋር እየተነጋገርን ነው ሲሉ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው አቶ እያሱ ሰለሞን ነግረውናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..



ወንድሙ ሀይሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page