top of page

ጥር 13፣ 2017 - በበጀት ዓመቱ አጋማሽ በ2,464 ሕገ ወጥ ግንባታዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ተናግሯል

  • sheger1021fm
  • Jan 21
  • 1 min read

በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ በ2,464 ሕገ ወጥ ግንባታዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ተናግሯል፡፡


ህገወጥ ግንባታ 2464፣ ህገ-ወጥ የመሬት መስፋፋት 11፣ ህገ-ወጥ የመንገድ ላይ ንግድ ከ27,000 በላይ ሰዎች አርምጃ ወስጃለሁ ብሏል፡፡


ከደንብ ተላላፊዎች ከ135 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስረድቷል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ደንብ ተላልፈው ከተገኙ ደንብ ተላላፊዎች ሰበሰብኩት ያለው ከ135 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግስት ካዝና ማስገባቱን ተናግሯል።


በህገ-ወጥ የመንገድ አጠቃቀም ከ5,000 ሰዎች በላይ መቅጣቱን የተናገረው ባለስልጣኑ ከህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ ደግሞ 821 ሰዎችን ቀጥቻለሁ ብሏል።


ከእነዚህ እና ከሌሎች ባለስልጣኑ ከሚቆጣጠራቸው ህገወጥ ድርጊቶች ከ135 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የሚናገሩት ዋና ስራ አስኪያጁ ያም ሆኖ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ግን በከተማዋ 58 በመቶ የደንብ መተላለፍ ቀንሷል ብለዋል።


ፋሲካ ሙሉወርቅ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page