top of page

ጥር 13፣ 2017 - በህገወጥ መንገድ ለግብይት ሊውል የነበረ ከ13,480 ሊትር በላይ ነዳጅ መያዙን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Jan 21
  • 1 min read

በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ ከ13,480 ሊትር በላይ ነዳጅ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ተናገረ፡፡


በክልሉ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትን ለማስቆም በአንድ ወራት በተሰራው ስራ በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 13,480 ሊትር ነዳጅ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውሏል ሲሉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን መናገራቸውን ሰምተናል።

ነዳጁ በቁጥጥር ስር የዋለው በኬላዎች ላይ በተደረገ ፍተሻና ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በሕገ-ወጥ መንገድ በቤት ውስጥ ተከማችቶ የተገኘ መሆኑን ተነግሯል።


በመኖሪያ ቤታቸው ደብቀው የተገኙ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።


ማርታ በቀለ

Comentários


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page