top of page

ጥር 13፣ 2017 - ሁለተኛው የኢንተርኔት ልማት ጉባኤ እየተካሄደ ነው

ጉባኤው በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነመንግስታት(IGAD) አባል ሃገራት ውስጥ የኢንተርኔት መሰረተ ልማት ቁጥጥር ማዕቀፎች ዙሪያ ውይይት እያደረገ ነው።


ኢንተርኔት አሁን ላይ በትምህርት፣ ጤና፣ ፋይናንስ ዘርፍና በሌሎችም ዘርፎች ላይ ትፅዕኖው እየጨመረ መጥቷል የተባለ ሲሆን የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ከዚህ ዘርፍ ለመጠቀም አብረው ሊሰሩ ይገባል ሲል ሰምተናል።


በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ የኢንተርኔት መሰረተ ልማት እጥረት፣ የሳይበር ሴኩሪቲ ችግር አለ፣ በሌላ በኩል ዘርፉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል ይህን እድል የአካባቢው ሃገራት በመጠቀም በጋራ የማልማት ስራ ሊሰሩ እንደሚገባ በጉባኤው ተነስቷል።


የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ የኢትዮጵያ መንግስት የቴሌኮም ዘርፉን ለግል ዘርፍ የከፈተው የበለጠ ለማሳደግ ነው ብለዋል።


ለ2ተኛ ጊዜ እየተካሄደ ያለው የኢንተርኔት ልማት ጉባኤ በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሙያዎችና አጥኚዎች ጥሩ ስራ እንዲሰሩ እድል ይሠጣል ተብሏል።


ጉባኤው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥር 15 ድረስ እንደሚቆይ ሰምተናል።


በረከት አካሉ

Comentários


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page